News & Events:

Peaceful Global Protest and Support for Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለኃይማኖት፤ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ለሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሰረት፤ ብፁዕ አቡነ አብረሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በትናትናው ዕለት ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም (January 23, 2023) በቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፤ ወደ ኢትዮጵያ የበረራ ጉዞ አድርገዋል። ሆኖም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም (January 22, 2023) ሦሥት ሊቃነ ጳጳሳት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የማያውቀውን ድብቅ ስብሰባ በማካሄድ፤ ከቀኖና ቤተክርስቲያንና አስተዳደራዊ መርህ ውጪ የፈፀሙት ድርጊት፤ በሀገረ ስብከታችን የሚገኙ ካህናትንና ህዝበ ክርስቲያኑን በእጅጉ አሳዝኗል። ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ድጋፉን ገልጿል። ጋዜጣዊ መግለጫውንም ከዚህ በታች ይመልከቱ።

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church the Arch diocese of Western Canada and Territories Press Release

His Grace Archbishop Abune Abreham EOTC Archbishop of the Diocese of Western Canada New Year Message
ስበር ዜና፤ ከዚህ በታች ያለዉን ወስፈንጥር (ሊንክ) ይጫኑ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሰጡት ማብራርያ የተሰጠ ምላሽ

Archbishop Abune Abraham Christmas Message
