ዜና ቤተክርስቲያን፤ News & Events
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የ፪ሺ፲፯ ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም (October 21, 2024) ተጀምሯል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል። ምልዓተ ጉባኤውን አስመልክቶ የወጡ መረጃዎችም ከዚህ በታች ቀርበዋል፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
የ2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ መግለጫ፤
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም የቀን ውሎ፤
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ/ም የአራተኛ ቀን ውሎ፤
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ/ም የቀን ውሎ፤
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ/ም የቀን ውሎ፤
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ፤ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም የተሰጠ መግለጫ።
የተወደዳችሁ የእግዚአብሄር ቤተሰቦች፤ እሁድ መስከረም 19 ቀን 2017 ዓ/ም (September 29, 2024) በኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ የመስቀል ማለዳ የቅዳሴ ስነስርዓት ላይ ተገኝታችሁ፤ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ጥሪያችንን አናስተላልፋለን።
"... God forbid that I should glory, save in the cross of our Lord Jesus Christ, by whom the world is crucified unto me, and I unto the world." (Galatians Chapter 6 : 14)
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church celebrating the Annual "መስቀል / Meskel" festival, the Holy National Holiday marks the finding of the true Cross that Jesus was crucified on. In 2013 UNESCO inscribed መሰቀል፤ Meskel (Cross) Holiday Celebration on the representative list of the intangible Cultural Heritage of Humanity.
We are cordially inviting you to attend our Live Mass on Sunday September 29, 2024 at the early morning hours.
Address; 11403 124 Street, Edmonton, AB, T5M 0K4
በኤድመንተን የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን፤ የቅዱስ ሚካኤል ጽዋ ማህበር አባላት፤ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ/ም (August 31, 2024) ያዘጋጁት የበጋ የመዝናኛ ፕሮግራም፤ በስኬት ተጠናቋል።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተላለፉ ወቅታዊ መረጃዎች፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
እንኳን ለእመቤታችን ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። ለጾመ ፍልሰታ (ሱባኤ) ቤተክርስቲያናችን ቅዳሜና እሁድ ማለዳ፤ ከ 6፡00 a.m. እንዲሁም ከሰኞ እስክ አርብ፤ ቀትር ከ12፡00 p.m. ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን እንገልፃለን።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የ2016 ዓ/ም ርክበ ካህናት፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፤ ግንቦት ፳፩ ፪ሺ፲፮ ዓ.ም (May 29, 2024) ተጀምሯል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል። ምልዓተ ጉባኤውን አስመልክቶ የወጡ መረጃዎችም ከዚህ በታች ቀርበዋል፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
የ2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ፤
የ2016 ዓ/ም ርክበ ካህናት፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፤ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ግንቦት ፳፩ ፪ሺ፲፮ ዓ.ም (May 29, 2024) የቀረበ የመክፈቻ ንግግር፤
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሳዔ በሰላም አደረሳችሁ። Happy Easter!
በብፁዕ አቡነ አብርሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡራኬ ስጭነት፤ ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ስባኪያነ ወንጌል፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና ምዕመናን በሚካፈሉበት፣ በወረብና ማህሌት የደመቀ ልዩ የትንሳዔ በአል ላይ፤ በኤድመንተን ደብረ ስላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ሚያዚያ ፳፮ ፪ሺ፲፮ ዓ.ም፤ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ (Saturday May 04, 2024, Starting from 08:00 pm) ከመላው ቤተሰብዎ ጋር ተገኝተው፤ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ፤ በክብር ተጋብዘዋል።
Join us celebrating religious holiday of Easter. We celebrate the Resurrection of Jesus Christ on Saturday May 04, 2024 starting from 08:00 pm., at Debre Selam Medhanealem Ethiopian Orthodox Church in Edmonton.
በሰሞነ ህማማት ቤተክርስቲያናችን ከጠዋቱ 8፡00 a.m. ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን እንገልፃለን።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ የወጡ ወቅታዊ መረጃዎች፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒዎርክና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ በመከልከላቸውና ወደ ሀገረ አሜሪካ እንዲመለሱ የተደረገበትን ምክንያት፤ ህገ ወጡ ቡድን ያወጣውን መግለጫ አስመልክቶ፤ ክኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ።
ይህን አንብበው፤ ለሌሎችም ያጋሩት ዘንድ በቤተክርስቲያን ስም እናሳስባለን።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ የወጡ ወቅታዊ መረጃዎች፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ፤ A call for Debre Selam Medhane Alem EOTC Members to attend Annual General Meeting
በኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ፤ እሁድ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ/ም (February 04, 2024) ከቅዳሴ በኋላ በቤተክርስቲያናችን ምድር ቤት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዚህ ዕለት የቤተክርስቲያናችን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው አጠቃላይ ሪፖርት የሚቀርብ ስለሆነ፤ አባላት ሁሉ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
We are cordially inviting all members of Debre Selam Medhane Alem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Edmonton to attend Annual General Meeting on Sunday February 04, 2024 after Divine Liturgy (Kidasse) Address: 11403 124 Street, Edmonton, AB, T5M 0K4
በኤድመንተን የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቢተክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ Board of Trustees
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ! Merry Christmas!
በብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የምዕራብ ካናዳ ህገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ፀሎተ ቡራኬና ትምህርተ ወንጌል፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት፤ በኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ቅዳሜ ታኅሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ/ም (January 6, 2024) ከምሽቱ 8:00 P.M. (20:00) ጀምሮ በልዩ መንፈሳዊ አገልግሎትና ኃይማኖታዊ ስነ ሥርዓት በድምቀት ይከበራል።
ስለዚህ እርስዎና ቤተሰብዎ በበዐሉ ዕለት ተገኝተው የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ፤ በአክብሮት መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
We are cordially inviting you to attend our Christmas Live Mass on Saturday January 6, 2024 from 8:00 P.M.
Address: 11403 124 Street, Edmonton, AB, T5M 0K4
በኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ቅዳሜ፤ ሕዳር 15 ቀን 2016 ዓ/ም (November 25, 2023) የተዘጋጀው ልዩ የስብከትና የዝማሬ መርሓ ግብር፤ በስኬት ተጠናቋል።
ከዚህ ዝግጅት የተገኘው ገቢ፤ ለታቀደው የቤተክርስቲያናችን የሕንፃ ግንባታ (ግዢ) ተግባር ላይ ለማዋል፤ በተከፈተለት ልዩ የቤተክርስቲያናችን አካውንት ይቀመጣል። ይህን የመጀመርያ ፈንድሬዚንግ ዕውን ለማድረግ፤ በኮሚቴና በግል ተሳትፎ እንዲሁም አስተዋፅኦ ላበረከታችሁ የእግዚአብሄር ቤተሰቦች ሁሉ፤ የመድኃኔዓለም ፀጋ፤ በረከቱና ጥበቃው አይለያችሁ።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ የወጡ ወቅታዊ መረጃዎች፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ/ም (October 30, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤
"... ከጌታችን ከእየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።" (ወደ ገላቲያ ሰዎች 6 : 14)
የተወደዳችሁ የእግዚአብሄር ቤተሰቦች፤ ሐሙስ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ/ም (September 28, 2023) በኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ የመስቀል ማለዳ የቅዳሴ ስነስርዓት ላይ ተገኝታችሁ፤ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ጥሪያችንን አናስተላልፋለን።
"... God forbid that I should glory, save in the cross of our Lord Jesus Christ, by whom the world is crucified unto me, and I unto the world." (Galatians Chapter 6 : 14)
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church celebrating the Annual "መስቀል / Meskel" festival, the Holy National Holiday marks the finding of the true Cross that Jesus was crucified on.
We are cordially inviting you to attend our Live Mass on Thursday September 28, 2023 and also on Sunday October 01, 2023 at the early morning hours.
Address; 11403 124 Street, Edmonton, AB, T5M 0K4
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ የወጡ ወቅታዊ መረጃዎች፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታን አስመልክቶ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ/ም (August 05, 2023) የተላለፈ መልዕክት
ዜና ቤተክርስቲያን፤ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ/ም (July 26, 2023 News from EOTC TV)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የ2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን አስመልክቶ የወጡ መረጃዎች፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Current information's and Press Releases
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከሰላምና የስምምነት ኮሚቴ፤ ስኔ 6 ቀን 2015 ዓ/ም (June 13, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤
ዜና ቤተክርስቲያን፤ ስኔ 6 ቀን 2015 ዓ/ም (June 13, 2023 News from EOTC TV)
ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ፤ የካህናት አባቶች ግድያን የሚመለከት፣ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ/ም (June 02, 2023 News from EOTC TV)
ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ፤ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ/ም (May 30, 2023 News from EOTC TV)
ከግንቦት 1 ቀን እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ/ም (May 09 - 24, 2023) ሲካሄድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማጠናቀቂያ መግለጫ፤
የግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ/ም (May 22, 2023) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የዘጠነኛ ቀን ውሎ መግለጫ፤
ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ/ም (May 18, 2023) የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ፤
የግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ/ም ዜና ቤተክርስቲያን (May 17, 2023 News from EOTC TV)
የግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ/ም (May 15, 2023) የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ ማብራርያ፤
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሳዔ በሰላም አደረሳችሁ። Happy Easter!
በብፁዕ አቡነ አብርሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡራኬ ስጭነት፤ ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ስባኪያነ ወንጌል፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና ምዕመናን በሚካፈሉበት፣ በወረብና ማህሌት የደመቀ ልዩ የትንሳዔ በአል ላይ፤ በኤድመንተን ደብረ ስላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ሚያዚያ ፯ ፪ሺ፲፭ ዓ/ም፤ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ (Saturday April 15, 2023, Starting from 08:00 pm) ከመላው ቤተሰብዎ ጋር ተገኝተው፤ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ፤ በክብር ተጋብዘዋል።
Join us celebrating religious holiday of Easter. We celebrate the Resurrection of Jesus Christ on Saturday April 15, 2023 starting from 08:00 pm., at Debre Selam Medhanealem Ethiopian Orthodox Church in Edmonton.
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፤ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም (March 30, 2023) በሕገ ወጡ የኤጴስ ቆጶሳት ሢመት የተሳተፉ አባቶችን ውግዘት ማንሳት የሚመለከት ጉዳይ፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፤ መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ/ም (March 29, 2023) ስለ ወቅታዊ ጉዳይ፤ "ቤተክርስቲያንና ይቅርታን" የሚመለከት ፋይዳ፤
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለኃይማኖት፤ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ለሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሰረት፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም (January 23, 2023) በቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፤ ወደ ኢትዮጵያ የበረራ ጉዞ ማድረጋቸው ይታወሳል። ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም፤ በኢትዮጵያ ተልዕኳቸውን ፈፅመው፤ የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ/ም (March 05, 2015) በሰላም ወደ ሀገረ ስብከታቸውና የመንበረ ጵጵስናቸው መቀመጫ፤ ኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተመልሰዋል። በዚሁ ዕለት ለኅዝበ ክርስቲያኑ፤ እናት ቤተክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጽናት የቆመለትን የዕምነት መርህና የአስተዳደራዊ ተመክሮ በተመለከተ ስፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያለው ኅዝብ፤ የቅዱስ ሲኖዶሱን ጥሪና አመራር ተከትሎ፤ ከዳር እስከ ዳር በመንቀሳቀስ ላደረገው ታላቅ ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
His Grace Archbishop Abune Abraham, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Archbishop of the Diocese of Western Canada and Territories interview released on March 23, 2023 by EOTC TV
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፤ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም (March 03, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፤ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም (March 03, 2023) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፤ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ/ም (February 18, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፤ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ/ም (February 11, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለኃይማኖት፤ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ለሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሰረት፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም (January 23, 2023) በቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፤ ወደ ኢትዮጵያ የበረራ ጉዞ አድርገዋል። ሆኖም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም (January 22, 2023) ሦሥት ሊቃነ ጳጳሳት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የማያውቀውን ድብቅ ስብሰባ በማካሄድ፤ ከቀኖና ቤተክርስቲያንና አስተዳደራዊ መርህ ውጪ የፈፀሙት ድርጊት፤ በሀገረ ስብከታችን የሚገኙ ካህናትንና ህዝበ ክርስቲያኑን በእጅጉ አሳዝኗል። ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ድጋፉን ገልጿል። ጋዜጣዊ መግለጫውንም ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ስበር ዜና፤ ከዚህ በታች ያለዉን ወስፈንጥር (ሊንክ) ይጫኑ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሰጡት ማብራርያ የተሰጠ ምላሽ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ጾመ ነነዌን አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
የነነዌን ጾምና ምህላ መጠናቀቅ አስመልክቶ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ/ም (February 09, 2023) ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፤ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም (February 15, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፤ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ/ም (February 17, 2023) የተሰጠ መግለጫ፤ Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod Press Release